አንዳንድ ነገሮች (ከፍጹም አቻም የለህ)

አንዳንድ ነገሮች

ዛሬ አማራ አማራ፣ አሮሞ ኦሮሞ፣ ትግሬ ትግሬ በማለትና የሞቱ የቆሰሉ ሰዎችን ፎቶግራፍ በመለጠፍ፣በውስጥ መስመር ይህ መጣልኝ፤ውሀ ተመረዘ፣ይህን አርጉ፣ ይህ የቤት አድማ… የትግል ስልት ትግሉን ይጎዳል ፤ወዘተ በማለትና እርስ በርስ አየተሞጋገስክ ብቻ ብዙ ቢልየን በዶላር ያለውን፤ብዙሺ የታጠቀ ከ40 ዓመት በላይ ፖለቲካ ሲሰራ የከረመ፤በጥላቻ ባህር የተጠመቀ፣ከአንተም ወገኖች በጥቅማጥቅም አታሎ ያጠመቀን የወየኔ ሰራዊትና ቡችሎችን እንደዚህ ልታሸንፍ አትችልም። ትግሉንም ታስመታለህ።ተጠንቀቅ።ከ11 ዓመት በኃላ እንደገና የተንቦገቦገውን የትግል ችቦ።እንዳታጠፋው ሰልት አውጣ፤ተደራጅ ።ይህን እንቅስቃሴ የሚመራ፣ አጭርና የረጅም።

ጊዜ እቅድ።የሚያወጣ አንድ ወጥ።መመሪያን የሚቀበል ደቦ ፍጠር…ከሰሜን እሰከ ደብብ ከምስራቅ እሰከ ምዕራብ።ያ ከሆነ ወሎ ለምን አልተነሳም ሸዋ ለምን ዝም አለ ብለህ ኣታላዝንም።(በነገራችን።ላይ ወላይታ፣ሲዳማ፣ጋሞ፣ከንባታ፣ሀዲያ፣ጉራጌ ፣ሀረሪ፣ሱማሌ: ለምን አልተነሳም?ተጠቀመ ማለት ነው?አንተም ለምን አልተነሳስ ብለህ አልጠየክም።) ትግራይን ግን አይነሳም ብለህ የደመደምክ ይመስላል…ስለተጠቀመ። አይደል?

የዚችን ሀገር ፓለቲካ እና የህዝባን ልብ ማወቅ ከባድ ነው።ስለዚህም ስራህም ከባድ ነው። የፖለቲካችን ባለቤቶች እኛ ብቻም አይደለንም።የዓለም የኢኮኖሚም ሆነ የፓለቲካ ሁኔታ፤የሀይል አሰላለፍ፤የአካባቢ ጸጥታ ሁኔታ፣ ከ40 ዓመት በላይ ተመጽዋችና ጥገኛ ኢኮኖሚያችንንም ከግምት ውስጥ አስገባ። ሰለዚህ ደንኳኑን ስፋ አርግ እንጂ አታጥብብ።ምስጢር አቀባይ ለማስከዳት ሞክር፤ወታደሩን አትተኩስ ብለህ ከተማጸንክ አንዱ እንኳ አዛዣቸው… ወያኔው.. ጀነራሉም ሆነ ኮለኔሉ ካንተ ወገን ይሆን ዘንድ ሰራ ስራ።ፓለቲካ ያለውን ሁኔታ መጠቀም አይደል እ ንዴ?ሰለዚህ ትግልህ ከሕዝብጋ ሳይሆን ባላንጣህ ከሆነው ህውሀትጋ ይሁን።ለይ።

ለምንድነው ትግሉ?

እኔ እንደሚመስለኝ ትግሉ ለ25 ዓመት ያለ ህዝብ ፍላጎትና እውቅና የተቀመጠው ህውሀትንና ጃንደረቦቹን መጣል ነው።ትግሉ ህዝብ ያልተስማማበት ህገመንግስትና ስርዓቱን ለመገርሰስ ነው። የመርዙ ፍሬ የሆኑትን ድንጋጌዎችና ውሳኔዎችን ከጥቅም ውጭ ማድረግ ነው።ትግሉ የሰብዓዊ መብትን ለማስከበርና ህልውናንና ክብርን ማስጠበቅ ነው።ሙስና መልካም አስተዳደር ምናምን አይደለም።የዛ ሁሉ ምንጭ የሆነውን የወያኔን ሥርዓት ማስወገድ ነው። ህገመንግስቱ ጥሩ ነው አትበለኝ።ይሄ ህገመንግስት ህዝብ ያለመከረበትና ያልተስማማበት ህገመንግስት ነው። የወያኔ የ”ትግል ውጤት”ና ፕሮግራም ባማረ ወረቀትና ባማርኛ መጻፉ ብቻ ሳይሆን ችግሩ ኢትዮጵያውያን የታገሉለትን የሕዝባዊ መንግስት በሕዝብ ለሕዝብ አላመጣም፤ በሀገራችን ጸንቶ የቆየውን የግል ንብረት የመያዝ፣ የመታጠቅ መብቶችና እና ሌሎች የተፈጥሮ ፀጋ የሆኑ ሰብዓዊ መብቶችና አያውቅም፤አያስከብርም፤አንዱ የመንግስት አካል አንዱን እንዲቆጣጠር አይፈቀድም፤ህገ መንግስቱን የሚተርጉምና ኢ-ህገመንግስታዊ የሆኑ ህጎችንና የመንግስት ትዕዛዞችን የሚቆጣጠር ብሎም የሚሽር ነጻ ህገመንግስታዊ የፍርድ ቤትን ማቋቋምን አይፈቅድም.. ወዘተ።

ህገመንግስትን ክልልና አጥር ሰለሰራልህና የራስ ህን ቋንቋ የሚናገሩ ግን አንደበላዮቻቸው መዝባሪ፣ በዳይና ገዳይ የሆኑትን የወንዝህን ልጆች ስላስቀመጠልህ የምትደገፈው ከሆነ ግን ተሳስተሀል። ሕገመንግስት ሩሶ እንዳለው ውል ነው- በመንግስትና በህዝብ መሀል።በነፃ ፍላጎት ውሉን ካልፈረምክ ይህ ህገመንግስት ያንተ ሊሆን አይችልም።የኔ ነው ተስማምቸ ነበር እንኳን ብትል 25 አመት ላንተና ለወገኖችህ ከለላ አልሰጠም። ልክ አንድ ፎቅ ብቻ ለመስራት የተቆፈረ መሰረት ላይ 10 ፎቅ ማቆም እንደማይቻል ሁሉ ይህን ህገመንግስት ይዞ አዲስ ሥርዓት ማምጣት ውሀ ቅዳ ውሀ መልስ ነው፤ወይም ለተጠባባቂ ነፍሰ ገዳይ መንገድ ማመቻቸት ነው።ስልዚህ ትግሉ ይህን መደርመስ ነው። ይህን ከደረመስን ማስተር ፕላን፤ የጸረ ሽብር ህግ ምናምን ተንኮታኩቶ ይቀራል።በዳዮች ለፍርድ ይቀርባሉ።

ግን

ወያኔ ይውደም ሰንል የትግራይ የሕዝብ ይውደም ማለታችን አይደለም።ወያኔን እናስወግድ ስንል የትግራይ ሕዝብን እናስውግዳለን ማለት አይደለም።በ4 ኪሎ፤በካዛንቺስ፣በባህር ዳር፤በናዝሬት፤ በአዋሳ፤በጋምቤላ፤በጎንደር፤በድሬዳዋ ወዘተ ብሎም በዛው በትግራይ ክፍለሀገር ተቀመጠው ሕዝብ ሳይፈለጋቸው የሚገዙትን ወያኔዎችን እና አገልጋዮቻቸውን፣ሰባአዊ መብት ረጋጮችንና ዘራፊዎችን ነው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ለማስወገድ የምንፈልገው።አነተም ይህ የጠፋህ አመስለኝም።

ስለዚህ ፊደል ለቆጠርከው ወንድሜ፣ ከተማ የተቀመጥከው ፣ገጠር የምትኖረው ፣ወጭ የምትኖረው እዛው ትግራይም ያለኸው ፤በየካፌው አማራና ኦሮሞ መጣብን የሚለውን ርካሽ የአባይ ጸሀየዬን፣ የበረከትንና የስዪም መስፍንን የደከመና የዘቀጠ ትንተናን አንተም ከምትተንትን ትግሉን ከለሌሎች ከወገኖችህጋ መቀላቀል እንካን ቢያቅትህ እጅህን አጥፈህ አተቀመጥ። እነሱ ዛሬ ተጠራርተው በየሚዲያው የሚማጸኑት ላንተና ለህዝባቸው አስበው አይደለም። ለምን እንደሚያደርጉት ታውቃለህ። ስለዚህ በአክሱም፣ በአድዋ፣ በሽሬ፣ በመቀሌና በተምቤን ያለውን ሕዝብህን አነሳሳ ወያኔን ጥሎ የራሱን የህዝባዊ መንግስትይመሰርት ዘንድ።ወያኔ ዛሬ ልክ በምስጥ የተበላ እንጨት ቤት አይነት ሆናል።የተነቃነቀው ነቅንቆ ይጥለዋል።አይ ጅሎ አትበለኝ። ይበላሀል ጅቦ።

ብሰል የበሰለው እስኪያር አትጠበቅ። ወያኔ በቅርብ ጊዜ ታሪክ ሆኖ ይቀራል።አነተ ግን ታሪክ መስራት ትችላላህ።ለመሬት ላራሹ፣ለብሔሮች መበት የሞተው ያማራ ልጅ ለራሱ ጥቅም አልነበረም።አነተ ቢያንስ ለሕዝብህም ጠቃሚ በኢትዮጵያ የሚገባውን ቦታ ያገኝ ዘንድ ታገል። ወያኔ አይደለሁም እያልክ እነሱ የሚሉትን እንደገደለ ማሚቶ አታስተጋባ።ምክንያትም አታብዛ። ሚናህን ለይ።የጀርመንም ሆነ የጣልያን ሕዝብ ሁሉ ለናዚዝምና ለፋሺዝም ተጠያቂ እንዳልሆነ ሁሉ የትግራይ ሕዝብ ለወያኔ ወነጀሎች፣ዝርፍያዎችና ኢሰባዊ ድርጊቶች ተጠያቂ አይደለም። አይሆንም።

ምንሊክ ፣ደርግ ምንትሴ እያልክ የወያኔና የሌሎች ደካሞችን መከራከሪያ ፍሬከርስኪ አታምጣብኝ። ይህ ታሪካዊ ጊዜ ነው።አንተም ለዚህ የሚመጥን ሰራ ስራ።ዝም ብለህ ምክንያት አትደርድር ፤ የሌላ ብሔር ታጋዮችን በድፍኑ አትጥላ።የማይሆን ስም አትስጣቸው።እነሱ አይደሉም እየገደሉና ሀገር እያጠፉ ያሉት።

“ንዴቴ እያለፈ ደሜ ሲቀዘቅዝ፣

ነገሩን በልቤ ዐስቤ ስተክዝ፣

የተናገረኝን ይህ ክፉ እብሪተኛ፣

ያመዛዝን ጀመር ዐሳቤ ሳይተኛ” እንዳለው ከበደ ሚካዔል አመዛዝን! ብሰል ።ተደራጅ ።

ኢትዮጵያዊው ሆይ ትግሉን በምትችለው መንገድ እርዳ።ልቦናህ የፈቀደውን ፤ወያኔን ሊጥል ወገኖችህን ሊታደግ የሚችል ድርጅት ውስጥ ተሳተፍ።በስራ ቦታ ፣ በየሻይና ቡና ቤቱ አታላዝን።በክርስትና በድግሱ በቤተክርስቲያን መስጊድ ስትገናኝ ስለሚደርሰው ነገር ከማውራት ባሻገርና ከንፈር ከመምጠጥ ባሻገር የምትችለወን አርግ።ይህ ታሪካዊ ጊዜ ነው።የታሪክ ተወቃሽ እንዳትሆን።ወያኔ ይውድቃል።ይህን የህዝብ ማዕበል የአባይ ፀሀዬ፣ የስብሀት፣ የበረከትም ሆነ የደብረፅዮን ከሜዳ ይዘው ያመጡት አሁን ግን የትላልቅ ንግድና የፎቅ ባለቤት ሆኖ ከተማ ውስኪ ሲጠጣ የሚውለው የወያኔ ጀነራል ሊያቆመው አይችልም።የህዝብ ማዕበል ይጠራርጋል።ሰለዚህ በጊዜ ተቀላቀል።ፈጣን ነው ባቡሩ።ተማመን።የጎንዮሽ ጉሸማውን አቁም።ወገንህ የሆነውን እከሌ እንዲህ ነው ምናምን እያልክ ወደታች አትውረድ።እግዚኦ ሕዝብህን አድን።

 

ገሞራው እንዳለው፥የኔ “ሀሳቤ ይኽ ነው፣

ለገባው ላይገባው፣

ላይገባው ለገባው፣

ሁሌ መተብተቡ ከቶ ምን ዋጋ አለው።”

ፍጹም አቻም የለህ ኣርሊንግተን ቨርጅንያ

Comments are closed, but trackbacks and pingbacks are open.