የትግራይ ህዝብና ህወሓትን ለይቶ በመመልከት ጉዳይ ላይ በተቃዋሚዉ መሐል የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ለማስወገድ የቀረበ ሃሳብ

የትግራይ ህዝብና ህወሓትን ለይቶ በመመልከት ጉዳይ ላይ በተቃዋሚዉ መሐል የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ለማስወገድ የቀረበ ሃሳብ:

1. ህወሓትንና የትግራይ ህዝብን በአግባቡ መለየት ዛሬ የአማራ ህዝብና የኦሮሞ ህዝብ መብታችን ተረገጠ ብለዉ በግንባር ቀደምትነት ትግል እያካሃዱ ይገኛሉ። ትላንት ደግም የትግራይ ህዝብ እንዲሁ አይነት ትግል አካሄዶ ነበር፣ መልሶ ሌላ ዓይነት ጭቆና ዉስጥ ሊወድቅ! የዛሬዉን ትግል አግባብንት አለዉ ብለን ስንቀበል የትግራይ ህዝብ ትላንት ላደረገዉ ተጋድሎ እዉቅና መስጠት የግድ ነዉ። ህወሓት/ኢሕአዴግ ጦርነቱን ይምራ እንጂ ድሉ የተገኘው የመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ደርግን ተማሮ ይሁንታዉን በመስጠቱና ሲችልም አብሮ በመዋጋቱ ነበር፣ ያለሱም የሚገኝ ድል ስላልነበረ የ1983 ድል የመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ነበር ማለት ትክክል ነዉ ብዬ አምናለሁ። በተመሳሳዩ የአድዋ ድል የአፄ ሚኒልክና ያስከተሉት መሳፍንትና መኳንንት ድል ብቻ አልነበረም፣ የመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ድል እንጂ። አፄ ሚኒልክ ከአድዋ ድል በኋላ አረመኔ መሪ ቢሆኑ ኖሮ በአረመኔነታቸዉ እንኮንናቸዋለን እንጂ የአድዋ ድልን አናንቋሽሽም። ወደ 1983 የህዝብ ድል ልመለስና፣ ከ1983 ኢትዮጵያ ከዳር እስከዳር በኢሕአዴግ የሥልጣን ማእቀፍ ዉስጥ እንድትጠቃለል ያደረገዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነበር፣ ይሁንታዉን በመስጠትና ትግሬ ነዉ ብሎ እንደባዕድ ሃይል ባለማየቱ! ሆኖም ግን በተለይ የመንግስት ስልጣንን ኢሕአዴግ ከተረከበበት ጊዜ አንስቶ የኢትዮጵያን ሕዝብ መብት፣ የትግራይን ህዝብ ጨምሮ፣ በየደረጃዉ ገፈፈ። ለዚህ በቡድን የተደራጁ የጥቂት ሰዎች ክፉ ተግባር የትግራይ ህዝብ ፈጽሞ ተጠያቂ ሊሆን አይችልም። ህወሓት የተከተለዉ የዘረኝነት ድብቅ ፖሊሲ የትግራይ ህዝብ ባለቤትም ተጠያቂም አይደለም። ትንሽ የታሪክ መጽሐፍትን ብናገላብጥ በ1983 ዓም ህወሓት ጋር ሲችል እየተዋጋ ያለበለዚያ ደግሞ በር እየክፈተ ህወሓት/ህወሓት/ 2ኛ ለአንድነት የቆመዉ የተቃዋሚ አጠቃላይ የትግል ስትራተጂ ሻዕቢያ ግብጽና ብዙ የአረብ አገሮች እንዲሁም አንዳንድ ጥቅማቸዉ ከሚነካ ኢትዮጵያ ብትፈርስ የሚመ ርጡ የህወሓትና የኢህአዴግ አባላትየኢትዮጵያን አንድነት የምንፈልግ ሰዎች ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ በሙሉ የሚያካትት የትግል ስትራተጂ ነድፈን፣ የሚያስፈልገዉን መስዋእትነት ከፍለን አገራችንን እንደ አንድ ሰላምንና መብትን አክባሪ፣ ህዝቦቿ ሰርተዉ፡ ተምረዉ፡ ያለሰቀቀን ወጥተዉ ገብተዉ፡ እምነታቸዉን አድርሰዉ፣ ከቤተሰብ ጋር ከዘመድ ወዳጅ ጋር እንደልብ ተገናኝተዉ፣የእለት ጉርሳቸውን አግኝተዉ የሚኖሩባት ተራ ሰላማዊ አገር ሁና ለማየት ከበቃን ጥሩ ጅምር ይሆናል። ይህ ትዉልድ በአንድንት ይሀን ማድረግ ከቻለ የሚቀጥለዉ ትዉልድ ደግሞ ለተራቀቀች ኢትዮጵያን መገንባት ይችላል። ይህን ሽግግር ለማድረግ ግን ሁሉን የሚያካትት የትግል ስትራተጂ የትግራይንም ህዝብ እንደሚጨምር ማስተዋል ይሻል። ከዚህም አኳያ የትግራይ ህዝብ ትግሉ ዉስጥ ዛሬ ተቀላቀለ፣አልተቀላቀለ፣ በትግራይ ህዝብ ላይ የተቀረዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ያለዉ ወንድማዊ ፍቅርና የዓላማ አንድነት አይቀየርም። ከሁሉ ባላነሰ እራሱን ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምነዉ የትግራይ ህዝብ ዝምታዉንም፣ፍርሃቱንም፣ግራ መጋባቱንም በትእግስት ተረድተን ከትግሉ ሜዳ እንዲቀላቀል ያላቋረጠ ጥሪ ማድረግን ስትራተጂዉ ይጠይቃል። አንዳንድ ጠባብ ተቃዋሚዎች የትግራይ ህዝብ የገባበትን ይህን የታሪክ አጣብቂኝን አላግባብ በመበዝበር “የትግራይ ህዝብ ተጠቃሚ ነዉ! ስርዓቱን ቢደግፈዉ ነዉ ዝም ያለዉ” በማለት በባዕድ አነጋገር፣ በአጸያፊ ቃላትም ሲሳደቡ ይሰማል።በመጀመሪያ ትክክል አለመሆናቸዉን ቀጥሎ ደግሞ ከኢትዮጵያአገራዊ አንድነት የየትግል ስትራተጂ ጋር የማይሃድ መሆኑን ማሳየት ይኖርብኛል። “የትግራይ ህዝብ ስርዓቱን ቢደግፈዉ ነዉ ዝም ያለዉ” የሚለዉ አባባል ከታሪክ መጽሃፍት ስንመለከት በደርግ ጊዜ የትግራይ ህዝብ ላይ ያ ሁሉ ግፍ (ከመደበኛ ጦርነት ሰለባ ከመሆን ያለፈ፣በአገር አንድነት ስም ግፍ ሲፈጸም)የት ነበር የተቀረዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ?ወይስ የተፈጸመዉ ተገቢ ነበር ብሎ ያምን ነበር ወይ?ወደ ኋላ ሄዶ ማንንም ለመኮነን አይደለም፣ ማንም ህዝብ በአምባገነኖች እጅ ዉስጥ እያለ ህሊናዉ የሚፈቅደዉን እንዳያደርግ ልጆቹንና ቤተሰቡን ሲል እንደሚፈራ፣ ከዛም አልፎ አንዳንዴ በጭንቀት ላይ ዘረኛ ፕሮፓጋንዳ ሲደገምበት በመደናገጥም ከጨቋኞች ጋር እንኳ ለአጭር ጊዜ ሊቆም እንደሚችል የኛም የዓለምም ታሪክ ይመሰክራል። በቅርብ ጊዜ እንኳ የኦሮሞ ህዝብ በመቶዎች በግፍ ሲገደል ድምጽ ማሰማት ያልቻለዉ የአማራ ህዝብ አንጀቱ ቢያርም በፍርሃትና ጥርጥር ቆይቶ የወልቃይት ሁኔታ ፍርሃቱን ቀደደለት። ይህም ሲሆን የወሎ፡የሽዋ አማራ እንዲሁም የተቀረዉ ብዙ የኢትዮጵያ ሕዝብ ገና የፍርሃት መጋረጃቸዉን አልቀደዱም። የትግራይም ህዝብ እንዲሁ! ኦሮሞና አማራዉ ህዝብ ፍርሀቱን ቀዶ እንደጣለዉ የትግራይም ህዝብ ፍርሃቱን የሚቀድበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም። ከዛ በፊት የሚያሳስበኝ፣ የራሳችንን ታሪክ በደንብ ሳናስተዉል፣ የትግራይን ህዝብ አለመነሳሳት ከመንግስት ጋር እንደመተባበር ተርጉመነዉ፣ ይህም የድላችንን ዕድሜ እንዳያራዝም፣ የኢትዮጵያ አንድነትንም አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ነዉ።ወንድም የሆነዉን የትግራይን ህዝብ ወደትግሉ ሳንታክት መጋበዝ እንጅ መግፋትና ማንጓጠጥ በእሳት መጫወት ነዉ! የኢትዮጵያ አንድነትን ይጎዳል፣ የኢትዮጵያ ጠላቶች እነሻዕቢያ፣ግብጽና የብዙ የአረብ አገር መሪዎች፣በአገር ዉስጥ ደግሞ ከሁሉም ዘውግ የተፈጠሩ ዘረኞችን ከማርካት ሌላ የሚፈይደዉ የለም። “ህወሓቶች ከአብራካችሁ የወጡ ልጆቻችሁ ስለሆኑ የትግራይ ህዝብ ልዩ ሃላፊነት አለበት” ብሎ ዛሬዉኑ ዉጤት መጠበቅ፣ ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚበልጥ የስሜታዉያን ደካማ አካሄድ ነዉ። የትግራይ ህዝብ በነፃነት የሚኖር ህዝብ ቢሆን ኖሮ ዛሬዉኑ በወሰነ ነበር። የትግራይ ህዝብ ከተቀረዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በበለጠ እንጂ ባላነሰ መብቱ እየተረገጠ፣ ከህወሓት ጥቂት ተጠቃሚዎች ጋር ስሙ ያላግባብ የሚጠፋዉ የሱ በመሆኑ፣ ሳናገለዉ ወገንተኝነትን በማሳየት ልናበረታታዉ የሚገባ ወገናችን ነዉ።、 ስለዚህም በተለይ ከትግራይ ህዝብ ጋር ለሚኖር የትግል አንድነት የሚከተሉትን ሃሳቦች አቀርባለሁ፡ 1ኛ የትግራይ ህዝብ ለ17 ዓመት አምባገነን ስርዓትን በመዋጋት ላደረገዉ ተጋድሎ እዉቅናን መስጠት፣ ህዝቡ የወየነበት ምክንያት ዘዉጋዊ ጭቆናን ማዕከል ያደረገ ብሶት በመሆኑ፣ የ1983 ድልም የአምባገነን ስርዓትን የገረሰሰ በመሆኑ የመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ድል እንደነበረ ያልተቀበልን ካለን መቀበል 2ኝ በተቃራኒዉ ደግሞ ለ17 ዓመት ዘዉጋዊ ጭቆናን ማዕከል ያደረገዉ በህወሓት የሚመራዉ ትግል፣ የፌዴራል ስርዓታችን ይመለስ ከሚል ባሻገር ሃገራዊ ግንጠላና ኢትዮጵያን ለማፈራረሰ (”የመቶ ዓመት የቤት ስራ ለመስጠት“) ዕቅድ ከነበረዉ ሻእቢያ ጋር በመግጠሙና የኢትዮጵያ አንድነት አደጋ ላይ በመጣሉ፣ ይህን ለመከላከል የኢትዮጵያ ሠራዊትና ህዝብ ለሃገሩ አንድነት ያደረገዉን ታላቅ መሰዋእትነትን ያልተቀበልን ካለን መቀበል 3ኛ የሌላዉን ዘዉግ፣ እምነት ወዘተ የተመለከተ ከመብት ጥያቌ ባሻገር፣ በጥላቻ ወይም ንቀት ማናቸዉንም ዛቻ፣ሰም ማጉደፍ በማንኛዉም ወገን ሲሰነዘር ያለቸልታ ፈጥኖ ማጋለጥ/ማስቆም 4ኛ የትግራይ ህዝብ አሁን በይፋ በተቃዉሞ ጎራ ባለመሰለፉ በአብዛኛዉ ተቃዋሚ ዘንድ የሚታየዉን አሉታዊ ትችት አግባብ እንዳልሆነና የሚያስከትለዉን ችግር ማስረዳት። በትግራይ አሁን በግለሰብ ደረጃ እየተደረጉ ያሉት ተቃዉሞዎችን በማበረታታት ወገናችን የሆነዉ የትግራይን ህዝብ ወደ ትግሉ እንዲቀላቀል የማያቋርጥ ጥሪ ማድረግ።

“ትግራይ-ለኢትዮጵያ” (Tigray Lethiopia – Face book name)